ቀን 1/3/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ በ2015 የትምህርት ዘመን እየተከናወኑ በሚገኙ ስራዎች ላይ ደስተኛ መሆኑን ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የ2015 የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተከናወኑ የትምህርት ልማት ዘርፍ ስራዎችን ገምግማል፡፡

በግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር፣ የቋሚ ኮሚቴ ጸሀፊ የተከበሩ ዶ/ር እመቤት ገዛህኝ ፣ የቋሚ ኮሚቴው አባል የተከበሩ ዶ/ር ጃራ ሠማ  እና የተከበሩ ዶ/ር ብሩክታዊት አደራ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች አቶ አድማሱ ደቻሳ እና አቶ ሳምሶን መለሰ ፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ እና የቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ እና የቢሮ ሀላፊ ቴክኒካል አማካሪ አቶ ደስታ መርሻ እና ሌሎች ባለሙያዎችም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የምልከታው አላማ አስመልክተው እንደገለጹት በ2015 የትምርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ዘርፍ ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን ለመፈተሸ እና የቀጣይ ስራ ውጤታማነትን ለማረጋገጥ እንዲያግዝ ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ሀላፊዋ አክለውም በየደረጃው በተካሄዱ ምልከታዎችም በከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት እጅጉኑ የሚያሰመሰግኑ እና ለውጥ የታየባቸው መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን በቀጣይም የትምህርት ተደራሽነትን ፣ ፍታዊነትን እና ጥራትን ለማረጋገጥ ምክር ቤቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ከ2014 የትምህርት ዘመን አፈጻጸም ግምገማ እና ከ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት እቅድ ዝግጅት ጀምሮ ስራዎች እየተገመገሙ እና የስራ አቅጣጫዎች እየተቀመጡ ወጥነት ባለው ደረጃ መከናወናቸው እንዳስደሰታቸው ገልጸው ተናቦ የመስራቱ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ የክለውም የሚታዩ ክፍተቶችንም በማረም ለላቀ ውጤት ቢሮው ሊተጋ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ቋሚ ኮሚቴው በቀጣይ የተሻሉ ስራዎችን ለመስራት እንዲቻል ላደረገው ምልከታ መስጋና አቅርበው በቀጣይ በቋሚ ኮሚቴው በኩል ቢሮው ሊታገዝባቸው የሚገቡ ጉዳችን ያነሱ ሲሆን የኮሚቴው አባላትም የሰጣቸውን አስተያየቶች በመውሰድ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s