ቀን 26/2/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኤች አይ ቪ ኤድስ  የዘርፈ ብዙ ምላሽ ቡድን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ስራ ክፍል ጋር በመተባበር ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ በዋናነት በትምህርት ቤቶች የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን መከላከል እና በስነ ተዋልዶ ጤና ዙሪያ የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ ከየካ ፣አዲስ ከተማና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የትምህርት ቤት መሻሻል ምክትል ርዕሳነ መምህራን፣የትምህርት ቤት ወተመህ ተወካዮች፣ከየትምህርት ቤቱ የጤና ባለሙያዎች የክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙ ጉዳይ ባለሙያዎችን ጨምሮ የከተማና ክፍለ ከተማ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮችና የሰላምና ጸጥታ ጽህፈት ቤት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲስተር ፈለቀች አንዳርጌ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የኤች አይ ቪ ኤድስ የበርካታ ወገኖቻችንን ህይወት የቀጠፈና ብዙ ህጻናትን ወላጅ አልባ ያደረገ ቫይረስ መሆኑን እና ትምህርት ቤቶች ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ አከባቢዎች መካከል የሚጠቀሱ በመሆናቸው ውይይቱን ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ማካሄድ ማስፈለጉን ገልጸው በአለም አቀፍ ደረጃ እስከ 2030 ኤች አይ ቪ ኤድስ ስጋት ወደማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የተያዘው እቅድ ስኬታማ እንዲሆን የትምህርት ማህበረሰቡ ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ ወይዘሪት ገንዘብ ደሳለ ኝ በበኩላቸው ውይይቱ የትምህርት ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል ፓኬጅን ተግባራዊ በማድረግ በተማሪዎች ላይ የፀባይ ለውጥ ማምጣት ከሚችሉ አካላት ጋር በሶስት ዙር እንደሚደረግና ከቀሪ ክፍለከተሞች ጋር በቀጣይ ተመሳሳይ ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመው ውይይቱ ተማሪዎችን ለአልባሌ ተግባራት ከሚያጋልጡ አዋኪ ጉዳዮች በመከላከል ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s