የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት “ጥቅምት 24 መቼም አንረሳውም!” በሚል መሪ ቃል አከበሩ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ የደረሰው ግፍና ጭፍጨፋ የመከላከያ ሰራዊታችን ኢትዮጵያን ለማቆም የከፈለው መስዕዋትነት እንደመሆኑ እለቱን መጪው ትውልድም እንዲዘክረው ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው ኢትዮጵያ ሁሌም እውነትን ይዛ የምትጉዋዝ ሀገር እንደመሆኑዋ አሁን ያለንበት የሰላም ደረጃ መድረስ መቻሉን አስገንዝበዋል፡፡
ዶክተር ዘላለም አክለውም የትምህርት ሴክተሩ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የሚወጣው ሚና ከፍተኛ እንደመሆኑ ሀገሪቱን መገንባትና ወደ ሚፈለገው ብልጽግና መውሰድ የሚችል ትውልድ ለመፍጠር ኃላፊነታችንን በአግባቡ ልንወጣ ይገባል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/