ቀን 24/2/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አጀማመርን በተመለከተ በትምህርት ተቋማት የተደረገ ሱፐር ቪዥን ግኝትን በተመለከተ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ውይይት አካሄደ።

በመርሃ ግብሩ ጥቅምት 24ትን መሰረት በማድረግ የህሊና ጸሎት በማድረግ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ መዝሙር በመዘመር የተጀመረ ሲሆን የድጋፍና ክትትል መርሀ ግብሩ ከመስከረም 9 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15/2015 ድረስ በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች፣በተመረጡ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶችና 64 በሚሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን በሂደቱም ከ200 በላይ የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ቡድን መሪ አቶ ፀጋዬ አሰፋ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ የድጋፍና ክትትል መርሀ ግብሩ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ታስቦ መካሄዱን ጠቁመው በድጋፍና ክትትል ሂደቱ የታዩ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የድጋፍና ክትትል ተግባሩ በትምህርት ቤቶችም ሆነ በወረዳና ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተካሄደው በክፍተት የሚታዩ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ ውጤታማ የመማር ማስተማር ስርዓት ለማስፈን እንደመሆኑ በዚህ ውይይት ተሳታፊ የሆኑ ርዕሳነ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮችን ጨምሮ የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በሱፐር ቪዥኑ የተሰጡ ግብረ መልሶችን ታሳቢ ያደረገ ስራ በመስራት የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s