ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮች የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮጀክትን ጎበኙ፡፡
የመስክ ምልከታው አራዳ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ገነት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን በጉብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በዋናነት በተገኙ ውጤቶች ላይ የልምድ ልውውጥ እንዲሁም በትምህርት ቤቱ ያለውን የትምህርት አሰጣጥ እንዲሁም የተማሪዎችን የማሸለቢያና የመመገቢያ ክፍሎች ከማየታቸው ባሻገር ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የሚሰጠውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ተመልክተዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/