የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳት ትምህርት ቢሮ እና የትምህርት እና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን በአፍ መፍቻ ቋንቋ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ላይ የፓናል ውይይት መድረክ በጋራ አካሄዱ፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ፣ የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ህይወት ጉግሳ እና ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ጥሩሰው እና የትምህርት ባለሙያዎች ፣ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ቴድሮስ ሽዋረገጥ ፣የግል ትምህርት ቤት ማህበር አመራሮች ፣ የግል ትምህርት ቤት ባለቤቶች እና አመራሮች ፣ የከተማው ወተማ፣ ወላጆች እና የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የመወያያ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር ባሉ ትምህርት ቤቶች በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ሂደት እና በስርዓተ ትምህርት አተገባበር እና በአፍ መፍቻ ቋንቋ አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ችግሮች በሚል ርዕስ በአቶ አድማሱ ደቻሳ እና በወ/ሮ ፍቅርተ አበራ በቅደም ተከተል ከቀረበ በሃላ በፕሮፌሰር ጥሩሰው እና በዶ/ር ቴድሮስ ሸዋረገጥ ወይይቱ እንዲመራ ተደርጋል፡፡
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ እና የትምህርትና ስልጠና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ማጠቃለያ የሰጡ ሲሆን ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ስራ ላይ ምን ችግሮች አሉ ፣ ችግሮች እንዴት ይፈታሉ ፣ በቀጣይ እንዴት መስራት አለብን የሚሉትን ጉዳዮች ለመመለስ መድረኩ የሚያግዝ መሆኑን ጠቅሰው የጋራ የሆነ አንድ ወጥ አስተሳሰብ ለመያዝ እና ቅንጅታዊ አስራር እንዲኖር መስል የውይይት መድረኮች ጠቃሚ ናቸው ብለዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/