ቀን 18/2/2015 ዓ.ም

ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል በሚያስችሉ ተግባራት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ክትትልና ትግበራ ዳይሬክቶሬት አማከይነት ለሁሉም የቢሮው ሰራተኞች በሁለት ዙር በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለት የመጀመሪያው ዙር ሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናውን ወስደዋል፡፡ 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ክትትልና ትግበራ ቡድን የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ ወይዘሪት ገንዘብ ደሳለኝ በስልጠናው ባስተላለፉት መልዕክት የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠርም ሆነ ለመከላከል በየደረጃው ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት በማስፈለጉ ለቢሮው ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸው በቫይረሱ የሚያዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥር አሁንም ቢሆን እየጨመረ ስለሆነ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ አካላትን ተጋላጭነት ለመቀነስ የአመለካከት ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ አስረድተዋል።

ባለሙያዋ አክለውም የትምህርት ሴክተሩ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ከፍተኛ ስራ መስራት ከሚጠበቅባቸው ተቃማት መካከል አንዱ መሆኑን ጠቁመው በትምህርት ቤቶች የሚገኙ  ተማሪዎች ለችግሩ ተጋላጭ እንዳይሆኑ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s