የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርዓተ ትምህርት ለመምህራን አስተዋወቀ።
በማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ ዘንድሮ ስርዓተ ትምህርቱ በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ከሚደረግባቸው በአማርኛ ከ22 እና በአፋን ኦሮሞ ከ22 በጥቅሉ ከ44 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጡ መምህራን እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ባለሙያ አቶ ነጋ ገረመው አዲሱ ስርአተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በሚደረግባቸው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ 500 የሚሆኑ የደረጃ 1፣2እና 3 መምህራን እንዲተዋወቁ መደረጉን ገልጸው መምህራኑም በስርአተ ትምህርቱ የተቀመጡ መርሀ ትምህርቶችንም ሆነ ይዘቶቹን በአግባቡ ተረድተው ለህጻናቱ ተገቢውን ዕውቀት ማስጨበጥ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት አስተባባሪ አቶ አለማየሁ ጣሰው በበኩላቸው በስርዓተ ትምህርት የማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ 309 የሚሆኑ የአፋን ኦሮሞ ቅድመ አንደኛ ደረጃ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቁመው መምህራኑ የሙከራ ትግበራ ከሚደረግባቸው ትምህርት ቤቶች የመጡ እንደመሆናቸው የመለማመጃ ደብተሩን ይዘትም ሆነ የመምህር መምሪያውን ተገንዝበው ተማሪዎቻቸው በአግባቡ ማስተማር እንዲችሉ በማሰብ የማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/