በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከጥቅምት 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቂያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ፡፡
ፈተናው በአዲስ አበባ በ9 የፈተና ጣቢያዎች ሲሰጥ መቆየቱን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ገልጸው ፈተናውን 24,987 ተማሪዎች መውሰዳችን አስታውቀዋል፡፡
አቶ ዲናኦል አክለውም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 47,520 የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የዘንድሮውን ፈተና መውሰዳቸውን ጠቁመው ፈተናውን ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ያልወሰዱና ተገቢ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተማሪዎች በቀጣይ እንደሚፈተኑ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል አቅጣጫ መቀመጡን አስረድተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጁ 9 የፈተና ጣቢያዎች 1600 የፈተና አስፈጻሚዎች ተሳታፊ መሆናቸውን አቶ ዲናኦል ገልጸው ፈታኞቹ ከተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች እንደመምጣታቸው ከተማ አስተዳደሩ የምግብና የመኝታ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/