ቀን 10/2/2015 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፈቱ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡራዩ ከተማ የተገነባውን የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት መርቀው ከፍተዋል።

የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤቱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ኢትዮጵያውያን ተሰጥኦዋቸውን የሚያወጡበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ በኢትዮጵያ በተለያየ ደረጃ ትምህርት ቤቶች  እና  ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በርካታ ባለተሰጥኦዎች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡

እነዚህ ባለተሰጥኦዎች  ያላቸውን ተሰጥኦ አበልጽገው ወደ ምርትና አገልግሎት ለመቀየር ሲያስቡ የትምህርት ቆይታቸውን ማጠናቀቅ ግድ ይላቸዋል፣ አሊያም ምቹ ሁኔታ ሳይፈጠርላቸው ባክነው ይቀራሉ።

ዛሬ የተመረቀው የተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤትም ይህንን ችግር የሚቀርፍ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ትምህርት ቤቱ  ባለተሰጥኦዎችን በመለየት ከመደበኛ መማር ማስተማር ሳይለዩ ልዩ ተሰጥኦዋቸውን የሚያበለጽጉበት  ነው ተብሏል፡፡

ህንጻው ማደሪያ፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የአስተዳደር ህንጻ ፣ የህክምና ማዕከል፣ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ ሙከራ ፣ ቤተ መጽሐፍ እና ወርክ ሾፖች ያሉት መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ሁሉንም አገልግሎቶች የሚሰጡ ግብዓቶች የተሟሉለት መሆኑ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s