እንኳን ደስ አለን!
አዲስ አበባ ‘በትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራም’ ምርጥ ተሞክሮ የ8ኛው የMUFPP (Milan Urban Food Policy Pact) ግሎባል ፎረም ዘላቂ አመጋገብ እና ስነ-ምግብ ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ ሽልማት አሸናፊ ሆነች።
አዲስ አበባ ይህንን ሽልማት ያገኘችው ጥቅምት 17/2022 (እ.ኤ.አ) በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ ” “Food to Feed the Climate Justice: urban food solutions for a fairer world “በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የ8ኛው የMUFPP ግሎባል ፎረም መድረክ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ133 ከተሞች ጋር ተወዳድራ በማሸነፏ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሰው የሚሰጥ ፖሊሲ በማውጣት እየተከናወነ ስላለው ሰው ተኮር ተግባራት ከMUFPP ፈራሚ ከተሞች ለመጡ ከንቲባዎች እና ተሳታፊዎች ልምድ አካፍለዋል።
በከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የተመራ የአዲስ አበባ ከተማ ልዑካን ቡድን እየተካሄደ ባለው “Food to Feed the Climate Justice: urban food solutions for a fairer world ” በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የ8ኛው የዓለም ፎረም ላይ በብራዚል ሪዮ ዴጄኔሮ እየተሳተፈች መሆኑን ከሜር ኦፊስ ያገኘነው መረጃ ያሳያል::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/