ቀን 8/2/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 ዓ.ም የአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎችን ጨምሮ የሁሉም የመንግስት 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን ተሳታፊ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ዝግጅትና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ በአንደኛ ሩብ አመት የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተ ሪፖርት አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳኘው ገብሩ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት በአንደኛ ሩብ አመት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው በትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርዓትን በማስፈን ለተማሪዎች ተገቢውን የትምህርት አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ በመጥቀስ በዚህ ሂደትም የርዕሳነ መምህራን ሚና የላቀ መሆኑን  አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው በውይይቱ በ2015 ዓ.ም አንደኛ ሩብ ዓመት በተከናወኑ ጠንካራ ተግባራትና በሂደት በታዩ ክፍተቶች ላይ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገብ እንዲቻል የሚያግዙ ሀሳቦች መነሳታቸውን ገልጸው በአንደኛ ሩብ አመት በርካታ ተግባራት ቢከናወኑም ከተማሪ ቁጥር ጀምሮ ያሉ የመረጃ አያያዝ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s