በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬው እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር በተገለጸው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዙር ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ያለምንም ችግር ተሰጥቶ ተጠናቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በነዚሁ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን ለመውስድ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬው እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪ ወደፈተና ጣቢያዎች ገብተው በዩኒቨርሲቲዎቹ ኦረንቴሽን ተሰቷቸው የፊታችን ማክሰኞ ፈተናውን መፈተን እንደሚጀምሩ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/