ቀን 4/2/2015 ዓ.ም

በልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት በተከናወኑ ተግበራት ዙሪያ አመታዊ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡

የምክክር መድረኩ በታርጌት ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ዲቭሎፕመንት አሶሴሽን (ECDD)አማካይነት የተዘጋጀ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በታርጌት ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ዲቭሎፕመንት አሶሴሽን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ፕሮጀክት ኦፊሰር አቶ ጥላሁን ተሾመ የውይይቱን አላማ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት የምክክር መድረኩ በየአመቱ በቢሮው የሚገኙ የስራ ክፍሎች ከአካቶ ልዩ ፍላጎት ትምህርት አንጻር አካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ የመማር ማስተማር ስርአት ለማስፈን በ2014ዓ.ም ከእቅድ ዝግጅታቸው ጀምሮ  ያከናወኑዋቸውን ተግባራት በመገምገም በዘንድሮው በጀት አመት የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል ታስቦ  መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ በምክክር መድረኩ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር በታርጌት ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ሴንተር ፎር ዲስኤቢሊቲ ዲቭሎፕመንት አሶሴሽን በከተማ አስተዳደሩ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርትን ውጤታማ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው ውይይቱ በቢሮው በሚገኙ ስራ ክፍሎች በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ በ2015 ዓ.ም የተሻለ ስራ ለመስራት የሚያስችል ግብአት የሚገኝበት እንደሚሆን አስገንዝበዋል፡፡

በምክክር መድረኩ በ16 ትምህርት ቤቶች ከልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት አንጻር የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገም የተደረገ የመስክ ምልከታ ሪፖርት ከመቅረቡ ባሻገር በትምህርት ቢሮ የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች የ2014 ዓ.ም አፈጻጸም ቀርቦ ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s