ዒድ ሙባረክ!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1497ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
1497ኛ የመውሊድ በዓልን ስናከብር የታላቁ ነቢይ ሙሐመድ ጽኑ አስተምህሮትና ለዓለማት የመላካቸው ምክንያት የሆነውን ርህራሄን ፣ እዝነትን ፣ ሰብእናን እና ቸርነትን በመጎናጸፍ እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ መሆን ይኖርበታል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የመውሊድ በዓልን ስናከብር ለመጀመሪያ ጊዜ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን እንዲወስዱ ልጆቻችንን ወደ ዩኒቨርስቲ በላክንበት ወቅት የሚከበረ በመሆኑ ፈተናዉ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ ሁላችንም የሚናችንን በመወጣትም ሊሆን ይገባል፡፡ ተፈታኝ ተማሪዎችም በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ጥሩ የመማማሪያ መድረክ የምታገኙበት እና መልካም የፈተና ጊዜ እንደሚሆንላችሁ እምነቴን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
በዓሉም የደስታ ፣ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የመተባበር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡
መልካም የመውሊድ በዓል!
ዒድ ሙባረክ!
ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/