በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በሁለት ዙር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዉ ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች ሽኘት የተደረገላቸዉ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት ወደ መፈተኛ ዩኒቨርሲቲዎች በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ የመፈተኛ ጣቢያዎች አንዱ በሆነዉ ኢ.ፌ.ዴ.ሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በተዘጋጀላቸው ተሽከርካሪ ወደፈተና ጣቢያዎች ገብተው በዩኒቨርሲቲዎቹ ኦረንቴሽን ተሰቷቸው የፊታችን ሰኞ ፈተናውን መፈተን እንደሚጀምሩ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል።
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/