ቀን 27/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ላይ ፈተናዉን ለማስተግበር ከተቋቋመዉ ኮማንድ ፖስት አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የመሩት ሲሆን በውይይቱ የቢሮው ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና የትራፊክ ጽህፈት ቤት አመራረችን ጨምሮ   የክፍለ ከተማ የትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎችና የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ዘንድሮ ፈተናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመስከረም 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደሚሰጥ ቀደም ብሎ በትምህርት ሚኒስቴር የተገለጸ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ፈተናውን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፤ ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ፤ ኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ፌደራል ቴክኒክና ስልጠና ኢንስቲትዩት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ዘንድሮ ፈተናው ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚሰጥ እንደመሆኑና የፈተናው ሂደትም በበላይነት በትምህርት ሚኒስቴር የሚመራ ቢሆንም  ከተማ አስተዳደሩ ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ 

ዶክተር ዘላለም አክለውም ቀደም ሲል ፈተናው ከሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቃማት አመራሮች ጋር መሰል ውይይቶች መካሄዳቸውን ገልጸው ቢሮው ከነገ ጀምሮ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ጣቢያ የሚያጋጉዙ ተሸከርካሪዎችን ማዘጋጀቱን በመግለጽ የጸጥታ አካላት ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲካሄድ የተለመደ ተግባራቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s