ከመዉሊድ በዓል ጋር ተያይዞ የ12ኛ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ቦታቸው የመግቢያ ቀን ላይ ማስተካከያ ተደረገ፡፡
መስከረም 28 የሚከበረውን የመዉሊድ በዓል አስመልክቶ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች በቀጣዩ ቀን ተገኝተው ስለፈተና የሚሰጣቸውን አጠቃላይ መግለጫ መከታተል እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው መስከረም 30 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሚጀምረው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መስከረም 26-28 ተጠቃለው በመግባት መስከረም 29 ስለፈተናውና ተያያዥ ጉዳዮች በየተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች ገለጻ የሚደረግበት ዕለት ነበር፡፡
ይሁንእንጂ የእስልምና እምነት ተከታዮች መስከረም 28 የመዉሊድ በዓል አክብረዉ መስከረም 29/2015 ዓም እሁድ ጠዋት መግባት እንዲችሉ በልዩ ሁኔታ የተፈቀደላቸዉ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ይህን ተከትሎም የፈተና እና ተያያዥ ጉዳዮች ገለጻ /Orientation/ ይህንን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እሁድ ከሰዓት በኋላ እንዲሰጥ ማስተካከያ መደረጉን በመግለጽ የእምነቱ ተከታይ ተማሪዎች ይህን አውቀው በተጠቀሰዉ ሰዓት በመገኘት ገለጻውን እንዲትከታተሉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
