ቀን 23 /1/2015 ዓ.ም

ትምህርት ሚኒስቴር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ላይ ማብራሪያ ሰጠ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የገለጹ ሲሆን ሂደቱ ተማሪዎች በራስ ጥረት ብቻ ውጤታማ የሚሆኑበት ነው ብለዋል።

ከዚህም መካከል የፈተናው ዝግጅትና ህትመት በቴክኖሎጂ ታግዞ በከፍተኛ ጥንቃቄና ከደህንነት ስጋት ነፃ በሆነ መልኩ መከናወኑን በመግለጫቸው  ተናግረዋል።

እስከ አሁን በነበረው የቅድመ ዝግጅት ሂደትም ከሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል መንግስታት የስራ ሃላፊዎች ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በመግለጫው ሀገር አቀፍ ፈተናው በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም በመጀመሪያው ዙር  የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች  ከመስከረም 30,2015 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 02,2015 ዓ.ም ፈተናውን ሲወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 8,2015 ዓ.ም እስከ 11,2015 ዓ.ም ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሏል።

ተፈታኞችም  ፈተናው ከሚሰጥበት ቀን በፊት ባሉት ሶስት ቀናት በሚፈተኑበት ዩኒቨርስቲዎች መገኘት እና ኦረንቴሽን መውሰድ እንደሚጠበቅባቸውም ተነግሯል።

ከፈተናው ቀን በፊት ባሉት ቀናት ተማሪዎችን ወደ ፈተና ቦታ የማምጣት እና ፈተናው እንዳለቀም ተማሪዎችን ወደየመጡበት አካባቢ የመመለስ ስራ እንደሚሰራም ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s