የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2014 ዓ.ም ማጠቃለያ ትምህርት ጉባኤ አካሄደ፡፡
የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽፈት ቤት በባለፈዉ ሳምንት በ2014 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በ2015 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ውይይት ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለት ጉባኤዉን የቀጠለ ሲሆን በጉባኤዉ ላይ የክፍለ ከተማዉ አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ በቀለ ጉታ ፣ የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ እና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በጉባኤዉ የመክፈቻ ንግገር ያደረጉት የአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ በቀለ ጉታ ሀገር የመቅረጽ ተግባር ሀገር በመገንባት ስራ ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚወስድ በመሆኑ በቀጣይም የትምህርት ዘመን ላይ ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ በበኩላቸዉ ጥናቶችን የሸልፍ ሲሳይ ከማድረግ ይልቅ የስራዎቻችን አጋዥ አድርገን ልንጠቀምባቸው ይገባል ብለዋል፡፡
በእለቱ የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት በትምህርት ስራ ላይ ያስጠናቸዉ ሶስት ጥናቶች ቀርበዉ ውይይት የተደረገባቸዉ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በበጀት አመቱ በክፍለ ከተማዉ የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ቡድኖች ፣ በተማሪዎች ውጤት የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ የወረዳ ት/ጽ/ቤቶች እና ትምህርት ቤቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የስራ ዘመናቸዉን በጥሮታ ላጠናቀቁም ርዕሰ መምህራን የሽኘት እና እውቅና የመስጠትም ተግባር ተከናውናል፡፡ ት/ጽ/ቤቱ በስራቸዉ ስራዎች ከጎኑ በመሆን እገዛ ላደረጉ ባለድርሻ አካላትም እውቅና ሰጥቷል፡፡
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
