እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን !
መስቀል የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ የስኬት ማሳያ ሲሆን ደመራ የሁለንተናዊ አንድነታችን እና ጥንካሬያችን መገለጫ በመሆኑ የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከብር በፍቅር በመረዳዳትና ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሚናችንን በመወጣት ሊሆን ይገባል፡፡
የዘንድሮ የመስቀልና የደመራ በዓል በ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት ልማት ስራችን ውጤታማ እንዲሆኑ በ2014 የትምህርት ዘመን በተከናወኑ አንኳር ተግባራት የተገኙ ዕመርታዊ የመማር ማስተማር ስራዎችን መለስ ብለን የተመለከትንበት እና በቀጣይ ስራዎቻችን ላይ ከመግባባት ላይ በደረስንበት በ29ኛዉ ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ማግስት የምናከብረው በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ቀደም ላከናወናችዋቸዉ አመርቂ ስራዎች መስጋናዩን እያቀረብቁ የትምህርት ልማት ስራ በአንድ አካል ጥረት ብቻ ውጤታማ የሚሆን ባለመሆኑ በቀጣይ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሚናችሁን ትወጡ ዘንድ አደራ እያልኩ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡
ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
