ቀን 15/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትላንትናው እለት ማካሄድ የጀመረውን 29ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ዛሬ አጠናቀቀ።

የትምህርት ጉባኤው  “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን በጉባኤው ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ፣መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወተማን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የቀጣይ የ2015 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን ከጠቀሳቸው የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል በአንዳንድ ተማሪዎች እና በአንዳንድ መምህራን ላይ በሚታዩ የስነ ምግባር ችግሮችን መቅረፍ፣ ውስጣዊ እና ውጫዊ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ማስወገድ ፣ የተማሪዎች የምገባ አገልግሎትን ለማዘመን መስራት እንደሚገባ ፣ የትምህርት ተቋማት ደረጃቸዉን እንዳሻሽሉ እና የሚሰጡት ትምህርት የጥራት ደረጃዉን በጠበቀ ደረጃ እንዲሆን በትኩረት መሰራት፣ የመምህራንን ፣ የባለሙያዎችን እና የትምህርት አመራሮችን አቅም የማጎልበት ፣ ትምህርትን በቴክኖሎጂ አግዞ መስጠት ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየት በመቀመር እና በማስፋት የትምህርት ተቋማት የመማማሪያ መድረኮች እንዲሆኑ ማድረግ እና የመረጃ አሰባሰብ ጥራትና ታማኒነትን ማዘመን የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በትምህርት ጉባኤው ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አብረውት በጋራ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር የትስስር ፊርማ በቢሮው ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ አማካኝነት የተፈራረመ ሲሆን በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በስራ አፈፃፀምና በተማሪዎች ውጤት የላቀ አፈፃፀም ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ለወረዳና ለክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እውቅና ከመሰጠቱ ባሻገር በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት ተቀብለዋል።

ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር በትምህርት ሴክተሩ በ2014 ዓ.ም ከተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስፍራ የሚሰጣቸዉ መሆኑን ጠቅሰዉ የትምህርት ማህበረሰበቡ አካላት ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅባቸዋል ብለዋለ፡፡

በትምህርት ጉባኤው ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አብረውት በጋራ ከሚሰሩ የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶ ጋር የጋራ ስራ ፊርማ ከተከናወነ በሀላ የጉባኤው የአቋም መግለጫ ቀርቦ የመርሃ ግብሩ ፍጻሜ ሆናል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s