ቀን 14/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 29ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ማካሄድ ጀመረ።

በጉባኤው መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ዋነኛው አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ የተዘጋጀው የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ዝግጅት መሆኑን ገልጸው በዚህ ሂደትም ከትርጉም ጀምሮ እስከ መጽሀፍ ዝግጅት መምህራንን በማሳተፍ የተሰራው ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን ወጪ ቆጣቢ በሆነና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ማጠናቀቅ ማስቻሉን አስረድተዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማሳደግ የትምህርት ግብዓት አቅርቦትን ጨምሮ  በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ መሻሻል መታየቱንና በዋናነትም በ8ኛ ክፍል ፈተና 64.07% የሚሆኑ  ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመው የዘንድሮው የትምህርት ጉባኤ በርካታ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት እንደመሆኑ በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚሆኑ ጠቃሚ ውይይቶች የሚነሱበት እንደሚሆን አስታውቀዋል።

የጉባኤው የክብር እንግዳና የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሪት ፋይዛ መሀመድ በበኩላቸው ትምህርት በዕውቀትና በስነምግባር የታነጹ ዜጎችን በማፍራት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ከተማሪዎች ምገባ ጀምሮ ዩኒፎርም፣ደብተርና ሌሎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ ምክር ቤቱም ለትምህርት ዘርፉ ውጤታማነት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አገንዝበዋል።

ጉባኤው ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀን የሚካሄድ ሲሆን የቢሮው የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2015 ዓ.ም እቅድ ፣የ2014ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና እንዲሁም የአዲሱ ስርአተ ትምህርት አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር በአመቱ ለትምህርት ስራው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ውጤታማ ለሆኑ ተማሪዎች ዕውቅና እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s