ቀን 14/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 29ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና!” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው በጠዋቱ ቆይታ ላይ የአዲስ አበባ ት/ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን የቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በአቶ ጌታውን ለማ በቢሮው እቅድ በጀት ዝግጅት እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና የ2014 ዓ/ም የተማሪዎች ውጤት ትንተና ሪፖርት በአቶ ዲናኦል ጫላ በቢሮ የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አማካኝነት ቀርባል፡፡

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ እና የከተማ አስተዳደሩ ተወማ ፕሬዝዳንት ኢንጂነር ጌታቸው ሰጠኝ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ኢንጂነር ጌታቸው ሰጠኝ በመልዕክታቸዉ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላቀ ደረጃ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወጡ እና የትምህርት ልማት ስራዉን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጎን የሚቆሙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ማህበራቸው ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረባቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጣቸው ያሉ በመሆናቸዉ የከተማ አስተዳደሩን አመስግነው በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ጥያቄዎች የሚሰጣቸዉን ጥያቄዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

በጉባኤዉ የከሰሀት ውሎም የቀረቡትን ሪፖርቶች መሰረት በማድረግ ውይይት በማናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በነገው እለትም በጋራ ለመሰራት ከተለያዩ ተቋማት ጋር የተስስር ሰነድ ፊርማ እና የተሸለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s