ቀን 12/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ለክፍለ ከተማና ክላስተር ሱፐር ቫይዘሮች ኦረንቴሽን ሰጠ።

ኦረንቴሽኑ በዋናነት የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከትምህርት አጀማመር ጋር በተገናኘ በአፋን ኦሮሞ ትምህርት በትምህርት ቤቶችና በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ የተሰጠ ነው።

በመርሀ ግብሩ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳስታወቁት በ2014ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ በተከናወኑ የተለያዩ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው በ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመንም አምና የተገ ኙ አበረታች ውጤቶችን መሰረት በማድረግ የትምህርት አገልግሎቱን ለማስፋፋት የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለውም የ2015 ዓ.ም ትምህርት በአብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች በአግባቡ ቢጀመርም አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ግን በሚፈለገው ደረጃ ወደ መማር ማስተማር ስራው እንዳልገቡ መረጃዎች መኖራቸውን ገልጸው በድጋፍና ክትትል ተግባሩ ተሳታፊ የሆኑ ሱፐር ቫይዘሮች በተዘጋጀው ቼክ ሊስት መሰረት ከክፍለ ከተሞችም ሆነ ትምህርት ቤቶች ተገቢውን መረጃ ይዘው መመለስ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሮቢ ዋሚ በበኩላቸው ሱፐር ቫይዘሮቹ በተመደቡባቸው ክፍለ ከተሞችና  ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ያህል ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ በቼክ ሊስቱ መሰረት ከአፋን ኦሮሞ ትምህርት አፈጻጸም ጋር በተገና  ኘ ተገቢውን መረጃ ይዘው እንዲያመጡ ታስቦ ኦረንቴሽኑ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s