የመስቀልና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላትን አከባበር አስመልክቶ ውይይት ተደረገ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በቀጣይ ቀናት ውስጥ የሚከበሩትን የመስቀልና የኢሬቻ የአደባባይ በዓላትን አከባበር በተመለከተ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዳል፡፡ በዓላቱ በሰላም ተጀምረው በሠላም እንዲጠናቀቁ የሰራተኛውን ሚና አስመልከቶ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በውይይቱ ላይ ሰራተኞች በአላቱ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቁ የማድረግ ኃላፊነት መውስድ እንደሚገባቸዉ ተመላክቷል፡፡
በውይይቱ ላይ ሰራተኞች ሰላምን የሚያደፈርሱ ከወትሮ የተለዩ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከቱ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ መስጠት እንዳለባቸው እንዲሁም ለሰላም ዘብ በመቆም ባዕላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸው ከመግባባት ላይ ተደርሳል ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳኛው ገብሩ ፣ የቢሮ ሀላፊ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ እና የቢሮ ሀላፊ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ሲሆኑ በንግግራቸው በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በበዓላቱ ተሳታፊ ስለሚሆኑ ሰራተኛዉ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸዉን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
