ቀን 8/1/2015 ዓ.ም

በአዲሱ የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚከናወኑ አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

በአዲሱ የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤቶች አካባቢ የሚከናወኑ አዋኪ ድርጊቶችን በመከላከል በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለማፍራት በትኩረት እንደሚሠራ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

በትምህርት ዘመኑ ከመማር ማስተማሩ ባሻገር የትምህርት ቤቶችን አካባቢ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት እንደሚከናወኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዚህም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያውኩ፣ መጠጥ ቤቶች እና መሰል ተቋማትን ተጽዕኖ የመከላከል ሥራ በስፋት ይከናወናል ብለዋል።

በ2015 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በተመረጡ በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር ይታወቃል።

በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የግብረ-ገብ እና የዜግነት ትምህርት እንዲሁም ለሥራ እና ክህሎት ሥልጠና ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም ዶ/ር ዘላለም ገልጸዋል።

በትምህርት ቤቶች አካባቢ ከአዋኪ ነገሮች በመከላከል በሥነ- ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር የትምህርት አመራሩ ግንዛቤ መውሰዱንም አብራርተዋል።

መልካም ስብዕና ያላቸውን ዜጎች ለማፍራት የወላጆች፣ የትምህርት ተቋማት፣ መምህራን እና ሌሎችም አካላት ተሳትፎ እና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።

በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ አዋኪ ድርጊቶችን በተደራጀ መልኩ መከላከል የሚያስችል ረቂቅ ሕግ በአገር አቀፍ ደረጃ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፣ ረቂቅ ሕጉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተናግረዋል።

ሕጉ ወደ ተግባር ሲገባም ችግሩን በመከላከል ረገድ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s