በ2015 የትምህርት ዘመን ውብ፣ ፅዱና ለመማር ማስተማር ምቹ በሆኑ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ለመቀበል ትምህርት ቤቶች የተሻለ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር የክፍለ ከተማው አመራሮች ትምህርት ቤቶች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል እያደረጉት ያለውን ቅድመ ዝግጅት ለመመልከት በትምህርት ቤቶች በመዘዋወር ምልከታ አድርገዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አበራ ብሩ በአካል ምልከታዉ ወቅት እንደገለፁት በአብዛኛቹ ትምህርት ቤቶች የ2015 በትምህርት ዘመን ውብ፣ ፅዱና ለመማር ማስተማር ምቹ በሆኑ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ለመቀበል የተሻለ ቅድመ ዝግጅት መኖሩን ጠቁመው በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ላይ የታዩ የቅድመ ዝግጅት ክፍተቶችን ከወረዳ አመራሮችና ከትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን ጋር ውይይት በማድረግ በአስቸኳይ የማስተካከል ስራ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በነገው ዕለት መስከረም 09/2015ዓ.ም በይፋ የሚጀመረው የ2015 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል በልዩ ትኩረት ምድረ ግቢን የማስዋብና የማጽዳት ስራዎች በማጠናቀቅ የመማር ማስተማር ሂደቱን በድምቀት ለማስጀመር የትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ዋና ስራ አስፈጻሚው አሳስበዋል።
አያይዘውም የተቋማቱ ግቢ ከግንባታ ተረፈ ምርትና ካቆረ ውሀ ነጻ ማድረግ በቀለምና ፈጠራን በመጠቀም ሳቢና ማራኪ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።
ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ትኩረት እንደተሰጠው ማሳያ እንደሆነና ሰላማዊና ምቹ ትምህርት ተቋማት እንዲኖር አመራሩ በትኩረት ሊከታተል እንደሚገባ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መዝገበ ይስማው ጠቁመዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት የመልካም አስተዳደርና አቤቱታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ቤካ በተመሳሳይ በመስክ ጉብኝቱ ተገኝተው አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
