ቀን 7/1/2015 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ያዘጋጃቸውን አዳዲስ የመማርያ መጻሕፍት በዛሬው እለት ይፋ ማድረጉንና እነኚህንም መጻሕፍት ርክክብ መፈፀሙ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን በዛሬው እለት በአንዳንድ አካላት በ4ኛ ክፍል የሂሳብ መፅሐፍ ላይ አለ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው ፅሁፍ በመሐሃፉ ላይ የማይገኝና የተሳሳተ ነዉ፡፡

ዛሬ ይፋ በተደረገውና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ4ኛ ክፍል የሂሳብ መጻሕፍት ገፅ 18 ላይ የግእዝ ቁጥርን አስመልክቶ ወጥቷል ተብሎ የተገለፀው ሃሳብ በመፅሐፍ ውስጥ የማይገኝ ሆነ ተብሎ የሃሰት መረጃ በማሰራጨት ውዥንብር ሊፈጥሩ በሚፈልጉ አካላት የተፈበረከ ነዉ፡፡ ይህንንም በዛሬው እለት መምህራኑ ራሳቸው በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ አረጋግጠዋል፡፡

እነኚህ አዳዲስ መጻሕፍት ከትምህርት መጀመር ቀደም ብሎ ህትመቱ ተጠናቆ  በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሰራጩ ያሉ   ሲሆኑ ህብረተሰቡም ከእንዲህ አይነት የተሳሳቱ ውዥንብሮች ራሳችሁን እንድትጠብቁ አደራ እንላለን፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s