ቀን 4/13/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ያዘጋጀውን የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ይዘት ለመምህራን ያስተዋወቀበትን መርሀ ግብር በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡

የመጽሀፍ ማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ በሁለት ዙር ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአማርኛና አፋን ኦሮሞ የትምህርት ዘርፍ ለሚያስተምሩ መምህራን በሁሉም የትምህርት አይነቶች በተዘጋጁ የመማሪያ መጽሀፍ ይዘቶች ዙሪያ ሲሆን ይዘቱን ቀደም ብሎ በመጽሀፍ ዝግጅቱ የተሳተፉ መምህራን ያስተዋወቁ ሲሆን ከመስከረም 3/2015 ዓ.ም ጀምሮ በመጽሀፍ ትውውቁ የተሳተፉ  መምህራን በየክላስተሩ በተመሳሳይ መንገድ ለሌሎች መምህራን  የመጽሀፉን ይዘት እንደሚያስተዋውቁ ከወጣው መርሀግብር ለማወቅ ተችሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በአማርኛው ስርአተ ትምህርት 5,040 የአንደኛ ደረጃ መምህራን በመጽሀፍ ማስተዋወቅ መርሀ ግብሩ ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸው የመጽሀፍ ትውውቁ መምህራኑ በይዘቱ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ይዘው  ወደ ማስተማር ስራው መግባት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ትግበራና አጠቃላይ ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሮቢ ዋሚ በበኩላቸው በመጽሀፍ ትውውቁ 3,540 በአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት የሚያስተምሩ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን ጠቁመው መጽሀፍ ትውውቁ መጽሀፎቹ አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርገው እንደመዘጋጀታቸው የመጽሀፍ ማስተዋወቂያ መርሀ ግብሩ  መምህራኑ ከመጽሀፎቹ ይዘትና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ የሚፈለገውን ግንዛቤ መፍጠር እንዲችሉ ያገዛቸው መርሀ ግብር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የመጽሀፍ ትውውቁ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ የትምህርት እርከኖች በተዘጋጁ የትምህርት አይነቶች የተካሄደ ሲሆን የትምህርት አይነቶቹም አማርኛ፤አፋንኦሮሞ፤እንግሊዘኛ፤ሒሳብ፤አጠቃላይሳይንስ፤አካባቢሳይንስ፤ሶሻልስተዲይ፤የዜግነት ትምህርት ፤ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ፤ አይ ቲ፤የስራና ቴክኒክ ትምህርት(career and technical education) እንዲሁም የክወናና እይታ ጥበባት ትምህርት(performing and visual arts education) ናቸው፡፡

አገልጋይነት ከእኔ ይጀምራል!

አገልጋይነት ለሀገር ክብር 

አገልጋይነት ክብርም፤ታላቅ ስብእናም ነው!

ዝቅ ብለን አገልግለን ፤ታላቅ ሃገር እንገነባለን!

ሀገርን ማገልገል ታላቅ ክብር ነው!!

ሀገሬን መቼም፣ የትም በምንም ሁኔታ አገለግላለሁ! 

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s