ቀን 1/13/2014 ዓ.ም
” ጳጉሜን በመደመር” በሚል መሪ ቃል የበጎ ፍቃድ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ መከበር ጀመረ።
በእለቱ በማለዳ በሁሉም ክፍለከተሞች አካባቢን ማጽዳት፤ ችግኝ ተከላና የተማሪዎች መማሪያ ክፍሎችን ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችንም ጨምሮ በጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ተገኝተው የበጎ ፍቃድ ቀንን የትምህርት ተቋሙን አካባቢን በማጽዳት አስጀምረዋል፡፡
ዛሬ አመቱን ሙሉ በበጎነት ስናከናውን የቆየነውን ተግባር የምናጠናቅቅበት ዕለት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዕለቱ ከሁሉም በላይ አሸባሪውን ህወሃት በከፈተብን ጦርነት ለኛ መኖር፤ ለኛ ሰላም እና ለሉአላዊነት ሕይወትቱ በመስጠት መስዋዕት እየከፈለ ያለን መከላከያ ሰራዊታችን እንዲሁም ጥምር ጦሩ እየሰጡት ላለዉ በጎነት ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ፡፡
የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር ራስን ከመስጠት ይጀምራል!
በጎ ፈቃደኝነት በገንዘብ የማይለካ ቀናነት ነው!
ያለንን ማካፈል የአብሮ መኖር ሚስጥር የበጎ ህሊና ማሳያ ነው!
ለሀገር ክብር የሚሰጥ በጎ ፈቃደኝነት ራስን አሳልፎ ለሌላ መስጠት ነው!
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/







