“ጳጉሜን በመደመር” ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ የማድረግ መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል መርሀ ግብር በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መካሄድ ጀምራል።
በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ደ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ፣ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደስ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ በጎነት የሁልጊዜ ተግባር መሆን እንደሚገባዉ እና ትምህርት ቤቶች ፅዱና ውብ እንዲሆኑ ለማድረግ የጽዳት ዘመቻዉ እገዛ እንደሚያደርግ መልዕክት ተላልፋል።
የበጎ ፈቃደኝነት ተግባር ራስን ከመስጠት ይጀምራል!
በጎ ፈቃደኝነት በገንዘብ የማይለካ ቀናነት ነው!
ያለንን ማካፈል የአብሮ መኖር ሚስጥር የበጎ ህሊና ማሳያ ነው!
ለሀገር ክብር የሚሰጥ በጎ ፈቃደኝነት ራስን አሳልፎ ለሌላ መስጠት ነው!
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/







