የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፕሮግራም ለፍትሃዊነት(GEQIP-E) በ2014 በጀት አመት የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት እቅድ አፈጻጸምና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
የውውይይቱን አላማ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት(GEQIP-E) ሲኒየር አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ከበደ በሰጡት አስተያየት ከአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ዓላማዎች አንዱ የትምህርት ፍትሀዊነትን እና ተደራሽነትን ማሻሻል እንደመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይህንኑ ግብ ለማሳካት ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በዚህም የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 46 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ መስጫ ማዕከላትን(resource center) በማቋቋም ለተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረጉን አስታውቀዋል።
አቶ አሸናፊ አክለውም ከአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ለፍትሀዊነት(GEQIP E) ፕሮግራም ለድጋፍ መስጫ ማዕከላቱ በጀት በመመደብ ማዕከላቱ በግብአትና በሰው ሀይል እንዲጠናከሩ ከመደረጉ ባሻገር በትምህርት ቤቶች የድጎማ በጀት አፈጻጸም መመሪያን መሰረት በማድረግ ማዕከላቱንየማጠናከር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በቀጣይም እነዚህ የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ተደራሽ ባልሆኑባቸው አከባቢዎች ተጨማሪ ማዕከላትን የማቋቋም ተግባር እንደሚከናወን አስረድተዋል።
በመርሀ ግብሩ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ከልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት አንጻር ስላለው ፋይዳ እንዲሁም ከትምህርት ቤቶች የድጎማ በጀት ለልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ስለሚደረገው ድጋፍ በአቶ አሸናፊ ከበደ ገለጻ ከመደረጉ ባሻገር የትምህርት ቢሮ የ2014ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP -E) የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት በጀት አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ባለሙያው በአቶ ዳንኤል አስራት የቀረበ ሲሆን በተጨማሪም የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት የአፈፃፀም ሪፖርት በርዕሳነ መምህራን ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ የክፍለ ከተማ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ተወካዮችና የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ካሉባቸው ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ የክፍለ ከተማ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/



