የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ፅሁፍ ቀረጻ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ያዘጋጀው የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ቀረጻ ላይ እንደሚገኝና ቀረጻውም በቅርቡ ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ስራው ዝግጁ እንደሚሆን ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በለጠ ንጉሴ ሂደቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት በማድረግ ከተዘጋጀው የተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ ለሬዲዮ መርሀ ትምህርት የሚሆን የይዘት መረጣ ተካሂዶ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች 900 ስክሪፕቶች ተዘጋጅተው በቀረጻ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
አቶ በለጠ አክለውም በአሁኑ ጊዜ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አንደኛ መንፈቅ አመት የሚያገለግሉ 450 የሚሆኑ ስክሪፕቶች ቀረጻ ላይ እንደሚገኙና በሂደቱም 75 የሬዲዮ ትምህርት ቀረጻ ፕሮግራም አዘጋጆችና ቴክኒሺያኖችን ጨምሮ የተለያዩ ጭውውቶችንና መዝሙሮችን የሚጫወቱ ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸው ቀረጻው ሲጠናቀቅ የአርትኦት ስራ ተሰርቶ ለትምህርት አገልግሎት እንደሚበቃ አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
