ቀን 24/12/2014 ዓ.ም

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋማት ቅድመ ዝግጅት በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን አስመልክቶ በዛሬው እለት በአንዶዴ ሁለተኛ ደረጃ ፣ በበሻሌ እና በጎሮ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት የተማሪዎች ምዝገባና የትምህርት ተቋማት ቅድመ ዝግጅት ያሉበት ደረጃ ምን እንደሚመስል ምልከታ አድርጓል።

በዚህም ምልከታ ተማሪዎች ምዝገባ እያደሩ ለመሆኑ ለመመልከት የተቻለ ሲሆን በመጪው የትምህርት ዘመን ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እየተሰሩ ለመሆኑ በበሻሌ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለማየት ተችላል።

በቅድመ ዝግጅቱም ትምህርት ተቋማትን ለተማሪዎች ሳቢ እና ማራኪ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ለማድረግ ክፍሎችን  የማስዋብ ፣ አጥርና ግቢዎችን የማሳመር ፣ ለተማሪዎች ምቹ ያልሆኑ መቀመጫዎችን የመጠገን እና በተቋማቱ ዙሪያ ያሉ አዋኪ ተግባራትን ለማስወገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን ሲደረጉ እንደቆዩ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በምልከታውም የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ጥሩ ጅማሮ ላይ እንዳሉ ለመመልከት መቻሉን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩም ወርቁ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s