ቀን 20/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ላለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ውይይት አጠናቀቀ።

በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ  የውይይቱ ተሳታፊዎች ያነሱዋቸው ሀሳቦች ለመድረክ ቀርበው ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በዋናነትም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የቅድመ ዝግጅት ስራው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ፣ ለተማሪዎች የሚሰራጩ ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ቢሆኑ፣በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚገኙ አዋኪ ጉዳዮች በተማሪዎች ስነ ምግባር ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ስለሆነ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ችግሩን መቅረፍ ቢቻል፣በማስፋፊያ አከባቢዎች  ያሉ የመማሪያ ክፍል እጥረቶችን መፍታት ቢቻል፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል መስራት እንደሚገባ እንዲሁም የትምህርት አመራሩን ሙያዊ ብቃት ማሻሻል የሚያስችሉ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ቢሰጡ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተው በቢሮው ኃላፊና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ምላሽ ተሰቷል።

በውይይቱ ማጠቃለያ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ውይይቱ የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ሀሳቦች የተነሱበትና የታለመለትን አላማ ያሳከ እንደነበረ ገልጸው ቢሮው በውይይቱ የተነሱ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት አስተባብሮ እንደሚሰራ አስታውቀዋል ።

ዶክተር ዘላለም አክለውም የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ የሚደረግበት ዓመት እንደመሆኑ ቢሮው ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የመማሪያ መጽሀፍና የመምህር መምሪያ አሳትሞ በቅርብ ቀናት ለትምህርት ቤቶች ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በሙከራ ትግበራ የተገኘው ልምድ በሙሉ ትግበራው ወቅት ውጤታማ እንድንሆን አስተዋጾው ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በውይይቱ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ  በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈቤት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከከተማ አስተዳደሩ መምህራን ማህበር ፣ ከወላጅ ተማሪ ማህበር እንዲሁም ከክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች ጋር በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በጋራ መስራት የሚያስችለውን የፊርማ ስነ ስርአት አካሂዷል ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s