ቀን 18/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2015ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሶስት ቀን የሚቆይ ውይይት ማካሄድ ጀመረ።

በመርሀ ግብሩ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገ ኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆን  ተሳታፊዎች ለመውያያነት በተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን ሰፊ ውይይት እንደሚካሂዱ የወጣው መርሀ ግብር ያሳያል።

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ በ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን አበረታች ውጤት መመዝገቡን እና እንደማሳያም በስምንተኛ ክፍል 63% የሚሆኑ ተማሪዎች ከ50% በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸው በዘርፉ ለተገኘው የላቀ ውጤት በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች አስተዋጾ ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋና እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ዶክተር ዘላለም አክለውም በተማሪዎቻችን ውጤት መሻሻል ላይ እየተመዘገበ የሚገኘውን አበረታች ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው በየትምህርት ተቋማቱ አከባቢ የሚገኙና በተማሪዎች ስነምግባር ላይ ችግር የሚፈጥሩ አዋኪ ጉዳዮችን ለመቅረፍ በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸው በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በተመረጡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚደረግና ለዚህም አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በበኩላቸው በትምህርት ሴክተሩ ከቅድመ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው በውይይቱ በአፈጻጸም የታዩ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችሉ ኃሳቦችን በማንሳት በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት በጋራ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s