ቀን 15/12/2014 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከወሎ ሰፈር ኡራኤል የተገነባው አዲሱ መንገድ እሁድ ቀን ከመኪና ነፃ ቀን(car free day) ለህፃናት አካላዊ እንቅስቃሴ በቋሚነት ዝግ እንዲሆን ተደረገ፡፡

የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም (early childhood program) በአዲስ አበባ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲደረግ የሚያስችል ውሳኔ ተወስኖ የህፃናትን ሁለንተናዊ እድገት የሚያጊለብቱ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ እንዳሉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም በፕሮግራሙ ከተካተቱት ስራዎች አንዱ የህፃናት አካላዊ እንቅስቃሴ እና መዝናኛ ስፍራዎችን የማዘጋጀት በመሆኑ የከተማው አስተዳደር በዛሬው እለት አዲስ የተገነባውንና ዘመናዊውን ከኡራኤል -ወሎሰፈር የሚወስደውን የ1.4 ኪሎሜትር የአስፋልት መንገድ በዛሬው እለት እሁድ እሁድ ከመኪና ነፃ ቀን(car free day) ለህፃናት አካላዊ እንቅስቃሴ በቋሚነት ዝግ እንዲሆን አድርጓል፡፡

እንቅስቃሴውን ያስጀመሩት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሲሆኑ የቀዳማይ ልጅነት እድገትና እንክብካቤ ፕሮግራም (early childhood program) አስተባባሪዎችና የከተማው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በዚህ ወቅት ከንቲባ አዳነች ባስተላለፉት መልእክት እንደተናገሩት ህፃናት ላይ ኢንቨስት ማድረግ አለብን ፤መዋያ ቦታዎች መጫወቻ ቦታዎች፤ልጆች ስለሃገራቸው እያወቁ የሚያድጉበት፤ የተሟላ አእምሯዊና ስነልቦናዊ እድገት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል ብለዋል፤

ለሁሉም ልጆች የምትመች አዲስ አበባን እንገነባለን!! ያሉት ከንቲባ አዳነች በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉ ልጆች ቤተሰቦች  ገቢ ይኑራቸው  ፤ ገቢ አይኑራቸው  በጎዳና ላይ የሚኖሩ ፤  ቤት ያላቸው የሌላቸው በአጠቃላይ  አዲስ አበባ ለሁሉም ልጆች ምቹ የሆነች እንድትሆን እንሰራለን ሲሉም ገልፀዋል፡፡

በዚህ ፕሮግራም 500 ባለሙያዎችም በአዲስ አበባ አስተዳደር ተቀጥረው  ወደ እያንዳንዱ ቤተሰብ በመሄድ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉም ከንቲባ አዳነች አስታውቀዋል፡፡

ዶክተር ታቦር ገ/መድህን የአዲስ አበባ ቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤና ድጋፍ ፕሮግራም አስተባባሪ በበኩላቸው፤የዚህ ፕሮግራም አላማ ልጆች የተሟላ ስነልቦናዊ አካላዊ እድገት እንዲኖራቸውና በደስታ ቦርቀው እንዲያድጉ ማድረግ ነው ያሉ ሲሆን ይህ ፕሮግራም ወደ ሁሉም ብሎኮች እና ቤተሰብ ድረስ የሚወርድ ፕሮግራም ነው ሲሉ መግለጻቸዉን የሜር ኦፊስ መረጃ ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s