ቀን 15/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት (GEQIP -E) የ2014 የበጀት ዓመት የአከባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተግባራትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሁለት ዙር ያካሄደውን ውይይት በዛሬው እለት አጠናቀቀ።

በውውይቱ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) የአከባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተግባራት ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በተጠናከረ መልኩ እንዲተገበሩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት ( GEQIP-E) ሲኒየር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ከበደ ገልጸው በመርሀ ግብሩ በዋናነት በትምህርት ሴክተሩ ከአከባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ጋር በተገናኘ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

አስተባባሪው የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም መርሀ ግብር ከአካባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተግባራት አንጻር እና የአካባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ መመሪያ ሰነዶች ገለጻ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት የአካባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በአቶ አሸናፊ ከበደ ቀርባል፡፡ በመርሀ ግብሩ የ5 ክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች የ2014 ዓ.ም የአከባቢና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በጀቱን ለታለመለት አላማ በማዋል በትምህርት ሴክተሩ የአከባቢና ማህበራዊ ጥበቃ ተግባራትን መሰረት አድርገው በሚከናወኑ ተግባራት ላይ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባ አቶ አሸናፊ በውይይቱ ማጠቃለያ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም የውይይቱ ተሳታፊ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች የ2014 ዓ.ም የአከባቢና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት የተካሄደ ሲሆን በጀቱን ለታለመለት አላማ በማዋል በትምህርት ሴክተሩ የአከባቢና ማህበራዊ ጥበቃ ተግባራትን መሰረት አድርገው በሚከናወኑ ተግባራት ላይ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባ አቶ አሸናፊ በውይይቱ ማጠቃለያ አስገንዝበዋል።

በውይይቱ ከትምህርት ቢሮ ፣ ከልደታ ፣ ከቂርቆስ ፣ ከአዲስ ከተማ ፣ ከለሚኩራ እና ከቦሌ ክፍለከተሞች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን ጨምሮ በአፈጻጸማቸው የተሻሉ የወረዳ የአከባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተወካዮች ተሳታፊ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ተመሳሳይ ውይይት ከቀሩት ስድስት ክፍለከተሞች ጋር  መካሄዱ ይታወቃል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s