የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት (GEQIP -E) የ2014 በጀት ዓመት የአከባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር የእቅድ አፈጻጸም ተግባራትን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።
በውውይቱ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) የአከባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተግባራት ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በተጠናከረ መልኩ እንዲተገበሩ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) ሲኒየር ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አሸናፊ ከበደ አስታውቀዋል። አቶ አሸናፊ አክለዉም የውይይት መድረኩ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት የተሳተፉ መሆናቸዉን እንዲሁም ውይይቱ በሁለት ዙር የሚከናወን መሆኑን በመግለጽ የዛሬዉ መድረክ የመጀመሪያ ዙር እንደሆነ ጨምረዉ አሳውቀዋል፡፡
አስተባባሪው የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም መርሀ ግብር ከአካባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተግባራት አንጻር እና የአካባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ መመሪያ ሰነዶች ገለጻ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት የአካባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን በአቶ አሸናፊ ከበደ ቀርባል፡፡ በመርሀ ግብሩ የ6 ክፍለ ከተማዎችና ወረዳዎች የ2014 ዓ.ም የአከባቢና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ትግበራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በጀቱን ለታለመለት አላማ በማዋል በትምህርት ሴክተሩ የአከባቢና ማህበራዊ ጥበቃ ተግባራትን መሰረት አድርገው በሚከናወኑ ተግባራት ላይ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባ አቶ አሸናፊ በውይይቱ ማጠቃለያ አስገንዝበዋል።
በመጀመሪያ ዙር ውይይት ከትምህርት ቢሮ ፣ ከኮልፊ ፣ ከየካ ፣ ከአቃቂ ፣ ከንፋስልክ ፣ ከቦሌ እና ከለሚ ኩራ ከክፍለ ከተማዎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን ጨምሮ በአፈጻጸማቸው የተሻሉ የወረዳ የአከባቢ እና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ተወካዮች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በነገዉ እለት የቀሩ ክፍለ ከተማዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል ።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!







