ቀን 13/12/2014 ዓ.ም

ከ2ሺ 900 በላይ ለሚሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ልዩ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየሰጠ መሆኑን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ውስጥ በሚገኙ ስምንት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ በ2014 የትምህርት ዘመን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ስነ-ምግባርና ውጤት ለማሻሻል እንደ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ጥናት መጠናቱን የገለፁት የጽ/ቤት ሃላፊዋ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ በጥናቱ ግኝት መነሻ የተሰጠው የመፍትሄ ሀሳብ ተማሪዎችን በተጠናከረ መልኩ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ውጤታቸውን ማሻሻል እንደሚቻል ያመላከተ በመሆኑ በመደበኛ ትምህርት ወቅት የሚሰጠው ማጠናከሪያ ትምህርት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ 10ኛ ክፍል መግባት ያልቻሉትን ተማሪዎች እና ከ8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል የተዛወሩትን በተመደቡበት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በክረምት መርሀ ግብር ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት አስፈላጎ ሆኗል ብለዋል፡፡

በዚህ መነሻነትም በአስኮ፣ በሚሊንየም፣ በኮልፌ፣ በድላችን፣ በአዲስ ከተማ፣ በየካቲት 23 እና በአቢሲንያ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በአጠቃላይ ለ2,908 ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርቱን በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ወ/ሪት ሳምራዊት ገልጸዋል፡፡

ሃላፊዋ አክለውም በተለይ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በክረምት ማጠናከሪያ መማራቸው የሚማሩበትን ት/ቤት አካባቢ በደንብ እንዲያውቁትና ከወዲሁ የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያግዛቸው ከመሆኑም በተጨማሪ ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርጉ ማንቂያ በመሆኑ ያልመጡ ተማሪዎችም ከላይ በተዘረዘሩት ት/ቤቶች በመገኘት ትምህርታቸውን መከታተል እንደሚችሉ ጥሪ እናስተላልፋለን ብለዋል፡፡

ከ9ኛ ክፍል በተጨማሪ በመጪው መስከረም 30/2015 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ላይ ከሚቀመጡት ውስጥ ለመማር ፈቃደኛ የሆኑትን 561 ተማሪዎችን እያስተማርን እንገኛለን ያሉት ሃላፊዋ  የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ትኩረት በመስጠት የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጥ በቁርጠኝነት ወደ ተግባር የገቡ ዋናና ምክትል ርእሰ መምህራን፣ በጎ ፈቃደኛ መምህራን እንዲሁም ውጤታቸውን እንዲሻሻል ለመማር ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎችን እናመሰግናለን ሲሉ መናገራቸዉን ከክፍለ ከተማዉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s