ቀን 11/12/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 የትምህርት ዘመን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ከክፍለ ከተማ ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ እንዳሳወቁት የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ላይ በተዘጋጀዉ ማስፈጸሚያ እቅድ መሰረት መከናወን እንዳለበት፤ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ በግል፣ መንግሰታዊ ባልሆኑ እና መንግስታዊ በሆኑ ትምህርት ተቋማት ላይ ሳይሸራረፍ እንዲተገበር ተገቢዉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ፤ የ2015 የትምህርት ዘመን አጀማመር የንቅናቄ ስራዎች ከቢሮ ተዘጋጅቶ በወረደዉ እቅድ መሰረት ማከናወን እንደሚገባ እንዲሁም የመጽሀፍ ስርጭትን በተመለከተ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በተማሪዎች እጅ እንዲደርስ ለማድረግ አጽኖት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ 

አቶ አድማሱ አክለዉም በ1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ላይ የሙከራ ትግበራ በ2014 የትምህርት ዘመን ላይ የተከናወነ በመሆኑ በ2015 የትምህርት ዘመን ሙሉ ትግበራ እንደሚካሄድባቸዉ ፤ በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም በከፊል በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ በ2015 የትምህርት ዘመን የሙከራ ትግበራ ከተከናወነ በሃላ በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ ፤ በ2015 የትምህርት ዘመን 6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፣ 8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ እንዲሁም 12ኛ ክፍል/የሁለተኛ ደረጃ የማጠቃለያ ፈተና ይስጣል ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በቅድመ ዝግጁት ስራ ውስጥ እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርትና የመጽሐፍ ህትመትና ስርጭትን በተመለከተ የተዘጋጀ ማስፈጸሚያ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s