የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ስልጠና እና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባውን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ ከግልና መንግስታዊ ካልሆኑ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ በጋራ አካሂደዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ ትምህርት ለአንድ ሀገር እድገት መሰረት መሆኑን በመጥቀስ አዲሱ ስርዓተ ትምህርትን በመተርጎም እና ወደ አዲስ አበባ ነባራዊ ሁኔታ በመቀየር እንዲዘጋጅ ተደርጎ ወደ ሙከራ ተግባራ ከተገባ በሀላ በሂደት የተገኙ ግብዓቶችን በማካተት ወደ ሙሉ ትግበራ በ2015 የትምህርት ዘመን ለመግባት ዝግጅት መጠናቀቁን አሳውቀዋል፡፡
አቶ አድማሱ አክለውም አዲሱ ስርዓተ ትምህርትን ሁሉም የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት እና መምህራን ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ እና የጥራት ደረጃውን ጠብቁ እንዲተገበር በሙሉ አቅም ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
መድረኩ በሁለቱ ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ መሆኑን የገለጽት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቀርተ አበራ የስርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ በ2015 የትምህርት ዘመን ላይ ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ እንዲተገበር በተለይም የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ ትምህርት ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግ እና ከዚህ ቀደም በስርዓተ ትምህርት ትግበራ ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማረም መስል መድረኮች ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በግል ትምህርት ተቋማት የስርዓተ ትምህርት አተገባበር ያለበት ሁኔታን በተመለከተ በወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንዲሁም የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የአጠቃላይ ስርዓተ ትምህርት ለውጥን በተመለከተ በአቶ አድማሱ ደቻሳ አማካኝት የመወያያ ሰነዶች በቅደም ተከተል ከቀረበ በሀላ ሰፊ ውይይት ተካሄዳል፡፡
በመድረኩ በከተማ አስተዳደር የሚገኙ ሁሉም የግል እና መንግስታዊ ያልሆኑ የትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ፣ የሁለቱም ተቋማት በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች እና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!








