የቦሌ ክፍለከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ308 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 47 ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
አሰሰተዳደሩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 22 የ60 ቀናት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የትምህርት ፣ የጤና ፣ የስፖርት እና ሌሎችም ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ፕሮጀክቶችን እንዳጠናቀቀ የክ/ከተማው የዲዛይንና ግንባታ ፅ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር አባይነህ ባጫ ገልፀዋል፡፡
በጊዜ ማዕቀፉ ፅ/ቤቱ ግንባታቸውን አጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ካደረጋቸው ፕሮጀክቶች መካከል
- መገኛው ወረዳ 13 የሆነውና ከ14 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወሰደው የቦሌ ሕብረተሰብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት G+4 ህንፃ፤
- የውለታ መጠኑ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነው የወረዳ 10 መሪ ትምህርት ቤት 3*1 ሜዳ፤
- በወረዳ 09 ውስጥ በብቸኝነት የሚገኘውና 30 ክፍሎች እንዲኖሩት ተደርጎ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የምስራቅ በር ቁጥር 2 አፀደ ሕፃናት፤
- 13 ሚሊዮን ብር የወጣበት ወረዳ 09 ጎሮ G +2 ቤተ-መፅሐፍት ጥቂቶቹ ሲሆኑ ሌሎችም ሰፊ ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው በርካታ ፕሮጀክቶች በፅ/ቤቱ ባለቤትነት ተገንብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!




