ቀን 7/12/2014 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት (GEQIP-E) የ2014 የትምህርት ዘመን እቅድ አፍጻጸም ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

በምክክር መደረኩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ቴክኒካል አማካሪ የሆኑት አቶ ደስታ መርሻ በአለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተዉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት መርሃ ግብርን በእቅዱ መሰረት ለመተግበር ባለመቻሉ ለአንድ ዓመት ተጫማሪ ተራዝሞ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰዉ በግምገማዉ ላይ መርሃ ግበሩ በምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ በጥልቀት በማየት የታዩ ክፍተቶች ካሉ በቀጣይ እቀድ ውስጥ በማካተት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የ2014 ዓ.ም የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት (GEQIP-E) የታለመለትን አላማ ስለማሳካቱ ለመመልከት መስል መድረኮች ጠቀሜታቸው የጎላ መሆኑን በማንሳት በስራ ሂደት ውስጥ የታዩ ክፍተቶችን በአግባቡ በማየት ለቀጣይ ስራ ውጤታማነት እንዲውሉ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡     

በምክክር በድረኩ ላይ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሃዊነት (GEQIP-E) በአራት የትኩረት ማዕከላት ላይ ውጤትን መሰረት ያደረገ የወጪ ስርዓት program for results (P for R)  የሚከተል እንደሆነ  አላማውም እንደ ሀገር የአጠቃላይ ትምህርት ፕሮግራሙን በተመረጡ አራት / የአጠቃላይ ትምህርት ውስጣዊ ብቃትን ማሻሻል ፣ የአጠቃላይ ትምህርት ፍትሀዊ ተደራሽነትን ማሻሻል ፣ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ማሻሻል እና በአጠቃላይ ትምህርት የተሻሻለ የአስተዳደር አቅም ማጎልበትን/ የትኩረት መስኮች ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ GEQIP-E ሲኒየር አስተባባሪ የሆኑት አቶ አሽናፊ ከበደ ተናግረዋል፡፡

አቶ አሽናፊ አክለውም ከፕሮግራሙ ውጤቶች አንጻር በ2014 በጀት አመት ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት መዋቅር አካላት ጋር በትግበራው ስለተመዘገቡ ውጤቶች ፣ በትግበራው ስላጋጠሙ ችግሮችና ወደፊት መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከባለደረሻ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት መከናወኑን ገልጸው በቀጣይ የ2015 በጀት ዓመት እቅድን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጸድቆ ሲወርድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ ይፈጠራል ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ ግብር ሰነድ ፣ የGEQIP-E የ2014 የትምህርት ዘመን አፈጻጸም ሪፖርት እና የየክፍለ ከተማዎች SIP እና ፋይናንስ የGEQIP-E የ2014 ዓ.ም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s