ቀን 6/12/2014 ዓ.ም

እንኳን ደስ አለን!

የሕዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡

የክረምት ወቅት መግባትን ተከትሎ ለሶስተኛ ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የግድቡ የውሃ ሙሌት በስኬት ተጠናቆ በአሁኑ ወቅት ውሃው በግድቡ አናት ላይ መፍሰስ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

አሁን ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሲቪል ስራዎች ግንባታ 95 በመቶ የደረሰ ሲሆን አጠቃላይ የፕሮጀክቱ አፈጻጸምም 83 ነጥብ 3 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 2ኛ ተርባይን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ስራ በትናንትናው ዕለት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

በትናንትናው ዕለት ስራ የጀመረው ዩኒት ዘጠኝ ሲሆን  ባለፈው የካቲት ወር ዩኒት10 ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የሚታወቅ ነው።  

ግድቡ አሁን ባለው ከፍታና በያዘው የውሃ መጠን ሁለቱ ተርባይኖች 540 ሜጋ ዋት ሃይል እያመነጩ ይገኛሉ።

ግድቡ በሙሉ አቅሙ ሃይል ማመንጨት ሲጀምር ደግሞ እያንዳንዱ ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ሃይል የሚያመነጭ ይሆናል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ዋናው ግድብ ከፍታ 145 ሜትር ሲሆን፥ ርዝመቱ 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ነው።

ግድቡ 1 ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ቦታ ስፋት የሚሸፍን ሲሆን፥ 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር የውሃ መጠን ይይዛል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s