ቀን 1/12/2014 ዓ.ም

የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ ሁኔታ ላይ ቁጥጥር እንደሚካሄድ ባለሥልጣኑ ገለጸ፡፡

የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ ሲያጠናቅቁ የቁጥጥር ሥራ በማካሄድ ከመመሪያ ውጪ ያልተገባ ክፍያ አስከፍለው የተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ።

አላግባብ የክፍያ ጭማሪን አስመልክቶ ከወላጆች የቀረቡ ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ የባለስልጣኑ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ እንደገለጹት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ ሲያጠናቅቁ ባለስልጣኑ ቁጥጥር ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ጠቁመዋል።

‹‹የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ምዝገባ ሲያጠናቅቁ ቁጥጥር ይካሄዳል፣ በመመሪያው መሠረት ያላግባብ ያስከፈሉ ካሉ ገንዘብ እንዲመልሱ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ አስተዳደራዊ ርምጃዎች ይወሰዳል›› ነው ያሉት።

በተደረገው አጭር ምልከታ 12 የግል ትምህርት ቤቶች ጭማሪን አስመልክቶ የወጣውን መመሪያ ጥሰው በመገኘታቸው ከመመሪያ ውጪ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለወላጅ መልሰው ሪፖርት እንዲያደርጉ መታዘዙንም ተናግረዋል።

በመመሪያ አተገባበሩ ላይ የተለያዩ ጥቆማዎች እየደረሱ ናቸው ያሉት ኃላፊዋ፤ አንዳንድ ተቋማት የምዝገባ ክፍያ መጨመር፣ በዓይነት መጠየቅ እና የመሳሰሉ ያልተፈቀደ ክፍያ ጭማሪ እያደረጉ እንደሚገኙ ጥቆማ ደርሶናል፤ ወርደን እያስተካከልን እንገኛለን ብለዋል።

ለክትትል የሚላኩ ባለሙያዎች አቅጣጫ ተሰጥቶአቸዉ እንደሚላኩ በመጠቆምም፤ ባለሙያዎች የተከፈለበትን ደረሰኝ ተመልክተው እንዲያረጋግጡ የሚያደርግ የመገምገሚያ ሰነድ ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።

ተግባሩ ባለሀብቶቹን ማነጋገር ብቻ አይደለም፣ ደረሰኝ ተመልክተው እንዲያረጋግጡ፣ ከተቻለም በየአንዳንዱ ተቋም የተወሰኑ ወላጆችን ማነጋገር የሚቻልበት አሠራር ተዘርግቷል ብለዋል፡፡

ከባለሙያዎች አቅም ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ ከተማ ያሉ ተቋማትን ለማየት በቅርንጫፍና በዋና መስሪያ ቤት ያሉ ባለሙያዎች በማሰማራት በሚገባ ለመገምገም ዝግጅት ተደርጓል። ከመመሪያው ውጪ ወርሃዊ የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ ማድረግና ሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን አስከፍለው በተገኙ ተቋማት ላይ ርምጃ ይወሰዳል፣ ለሕዝብም ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

በአብዛኛው እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ምዝገባ የሚጠናቀቅ በመሆኑ ከነሐሴ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማትን በመዘዋወር የሚደረገው ምልከታ ያላግባብ ክፍያ የተቀበሉ የትምህርት ተቋማት ገንዘብ እንዲመልሱ ከማድረግ ጀምሮ አስተዳደራዊ ርምጃ የሚወሰድ ይሆናል።

‹‹ከመደበኛ ክፍያ ውጪ በየትኛውም መልኩ ክፍያ ማስከፈል አይቻልም፣ አንድ የትምህርት ተቋም ፍቃድ የተሰጠው ለማስተማር እንጂ፤ መጽሐፍም ሆነ ደብተር መሸጥ አይችልም። ከተሰጠው ፍቃድ ውጪ የተንቀሳቀሰ ተቋም ከተገኘ ርምጃ ይወሰድበታል›› ብለዋል።

መመሪያው በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምንም ዓይነት ጭማሪ እንዳያደርጉ እንደሚያዝ አስታውሰዋል።

አምና ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ መጨመር እንደማይችሉ ለመቆጣጠር የማስፈጸሚያ መመሪያ ተዘጋጅቷል። ዓላማው የኅብረተሰቡ የመክፈል አቅም፣ የኑሮ ውድነት ችግርን ታሳቢ ባደረገ መልኩ አምና የጨመሩ ተቋማት እንዳይጨምሩ ለማድረግ ነው ሲሉም መናገራቸዉን ኢ ፕ ድ ዘግባል ።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s