የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ዝግጅት ተጀመረ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት ለተማሪዎች ድጋፍ የሚያደርጉ የሬዲዮ ትምህርቶችን ማዘጋጀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሂደቱም የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ዝግጅት ላይ መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በለጠ ንጉሴ ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጌታቸዉ ታለማ በበኩላቸዉ የሬዲዮ ትምህርት ይዘት መረጣ ተጠናቆ ወደ ስክሪፕት ጽሁፍ ዝግጅት ሂደት ላይ መደረሱን በማንሳት የሬዲዩ ትምህርት ስክሪፕት ዝግጅቱ እስከ ነሐሴ 14 ደረስ ቆይታ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ስርዓተ ትምህርትና ሱፕርቪዥን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሮሚ ዋሚ በበኩላቸዉ በሁለቱም የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች በመዘጋጀት ላይ የሚገኘዉ የሬዲዮ ትምህርት የስክሪፕት እንዴት ይዘጋጃል ፤ ምን ምን ርዕሰ ጉዳዮችን ያካታል በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ገለጻ በባለሙያዎች ከተሰጠ በሀላ ወደ ጽሁፍ ዝግጅቱ መገባቱን ተናግረዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
