በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በአስኮ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተካሄደ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ውስጥ ከ30 ሺህ በላይ የፍራፍሬና የተለያዩ አገር በቀል ችግኞችን በክረምት መርሀ ግብር መትከል መቻሉ ተገለጸ፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በ2014 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተናቸውን ወስደው ወደ 9ኛ ክፍል የተዘዋወሩ ተማሪዎች በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ሚገቡባቸው ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመገኘት ችግኝ እየተከሉ ሲሆን አላማውም የተከሏቸውን ችግኞች በቅርበት ሆነው እንዲንከባከቡ ለማድረግ መሆኑን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሪት ሳምራዊት ቅባቱ አሳውቀዋል፡፡
ሀላፊዋ አክለዉም ችግኞችን ከመተከል በዘለለ በቅርበት ሆኖ መንከባከብ ላይ ማተኮር እንደሚገባ በክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት በአስኮ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባዘጋጀው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር ላይ ተናግረዋል፡፡
በክረምት በበጎ ፈቃደኛ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና መምህራን የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርቶች እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎች በክፍለ ከተማዉ የትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድ ተጠናክረው እየተሰሩ መሆኑን ያገኘነዉ መረጃ ያሳያል፡፡
