በተማሪዎች ማርች ባንድ መካከል ልምድ ልውውጥ ተካሄደ፡፡
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች ማርች ባንድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኘዉ ሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ከሚገኘዉ የተማሪዎች ማርች ባንድ ጋር ልምድ ለውውጥ አካሄዳል፡፡
በልምድ ልውውጡ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ አስራት ሽፈራዉ መሰል ተግባራት መጠናከር እንዳለባቸዉ በመግለጽ ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተማሪዎች ማርች ባንድ እዚህ ድረስ በመምጣት ላካፈለዉ ልምድ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የልምድ ልውውጡ ብዙ ያስተምረናል ያሉት አቶ ግርማ ገመቹ የሚኒሊክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች ማርች ባንድ ረዳት አስልጣኝ ናቸዉ፡፡ አቶ ግርማ አክለዉም የአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳር ትምህርት ቢሮ በቀጣይ የተማሪዎችን ማርች ባንድን ለማጠናከር ሰፊ ድጋፍ እንደሚያደርግ እምነቴ ነዉ ብለዋል፡፡
በልምድ ልውውጡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሙዚቃ ስርዓተ ትምህርት ባለሙያ እና የማርች ባንድ መስራች እና አስልጣኝ የሆኑት አቶ ዳንኤል ታደሰ ብሩ እና የተለያዩ ሙዚቀኞች አነቃቂ ንግግር እና መልዕከት ለሁለቱም የተማሪዎች ማርች ባንድ አባላት አስተላልፈዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: – aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/
ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!






